ዳሂ መቆፈሪያ መኪና

የመጠየቂያ ቅጽ

የላይኛው መዋቅር ከፍተኛ የሀይድሮሊክ አሰራርን እንዲመጥን፣ የኬዝ ድንቅ የእድሜ ቆይታ እና በአስቸገሪ ሁኔታ ውስጥ እንኳን አስተማማኝነቱን እንዲያረጋግጥ ተደርጎ እንደ አዲስ ዲዛይን የተደረገ ነው፡፡

 

 

ለረጅም ግዜ ተብሎ የተሰራ

የላይኛው መዋቅር ከፍተኛ የሀይድሮሊክ አሰራርን እንዲመጥን የኬዝ ድንቅ የእድሜ ቆይታ እና በአስቸገሪ ሁኔታ ውስጥ እንኳን አስተማማኝነቱን እንዲያረጋግጥ ተደርጎ እንደ አዲስ ዲዛይን የተደረገ ነው፡፡ ከፍ ያሉና ጥልቅ ተደርገው የተሰሩ ብራኬቶች እና ለቁሳቁሶቹ ረጅም እድሜ የመቋቋም አቅም ያለው እና የመውረጃ ሰአት ያነሰ፡፡ በጥልቅና በከፍተኛ ደረጃ የተገነቡት የጎን ግድግዳዎች የጭረት እና ፍቀት መጠን እና ሰርቪስ የማድረጊያ ጊዜ ለመቀነስ ይረዳሉ፡፡ አዲሱ ባለ ሰንተቲክ ሀይድሮሊክ ፊልትሮ ስርአቱ እንዳይበከል የሚረዳና የሰርቪስ ማድረጊያ ወጪን ለመቀነስ እና የማሽኑን ረጅም እድሜ ለመስጠት የሚያግዝ ነው፡፡

ዝቅተኛ የማሰሪያ (ኦፕሬት) ማድረጊያ ወጪ
የነዳጅ አጠቃቀም ብቃቱ የተረጋገጠለት ሞተር ዝቅተኛ የነዳጅ ፍጆታ ስላለው የቲየር ሶስት ልቀት መመሪያዎችን ያሟላል፡፡ ትልቅ የነዳጅ ጋን መኖሩና የነዳጅ ፍጆታው ዝቅተኛ በመሆኑ አንዴ በተሞላው ነዳጅ ከሁለት ቀን በላይ መስራት ይቻላል፡፡ የተሻሻለው የመጠገኛ ስርአት በሁሉም እንዝርቶቹ ላይ ግራሶ የመጨመሪያ ጊዜ እንዲራዘም ያደርጋል፡፡ ሁሉም ፊልትሮዎችና በመደበኛነት ነዳጅና ቅባት መጨመሪያዎቹ በቀላሉ ተደራሽ ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡ ራዲያተሩና ማቀዝቀዣው ቀልጣፋ የማቀዝቀዝ ሁኔታ እንዲኖርና ለማፅዳት በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን ተደርጎ ጎን ለጎን የተገጠመ ነው፡፡ በአማራጭነት ከፍተኛ ፍሰት ያለው የነዳጅ መሙያ ቱቦ ከነአውቶማቲክ መዝጊያው ጋር የተገጠመለት በመሆኑ ለመደበኛ ነዳጅ አሞላል ጊዜ ይቆጥባል፡፡

ጉልበት እና ፍጥነት
በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሎ የተሰራው የሀይድሮሊክ ስርአት ከፍተኛ የመተጣጠፍ ጉልበት፣ የተሻሻለ የሽክርክሪት ፍጥነት እና የተሻለ እንቅስቃሴ ፍጥነት በመስጠት ሶስት የአሰራር ዘዴዎች ያሉት ሲሆን ፈጣን የዙር ጊዜ የሚስገኝና ምርታማነትን በ5 በመቶ የሚያሳድግ ነው፡፡ የጉልበት መጨመሪያው አውቶማቲክ የተገጠመለት ነው፡፡ የፍጥነትና ጉልበት ኤሌክትሮኒክ መቆጣጠሪያ መኖሩ የነዳጅ ፍጆታ እንዲቀንስና ከምርት ውጤት አንፃር ከፍተኛ የምርታማነት ጥቅም እንዲኖር የሚያስችል ነው፡፡

የኦፕሬተር ምቾት

ሰፊ የጋቢና መዋቅር ለእግርና ለመረገጫ ሰፊ ቦታ ያለው ሲሆን ሰፊው የመስታወት አካል ለኦፕሬተሩ መልካም እይታን ይፈጥራል፡፡ ምቾት ያለው ንድፉ አምቺ መቆጣጠሪያ እና ዝርግ መቀመጫው ለሁሉም ኦፕሬተሮች መልካም ምቾት ይፈጥራል በተጨማሪም ለስላሳ የጋቢና መግጠሚያ ፈሳሾች እና እጅግ ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ ሽፋን ለኦፕሬተሩ መጨናነቅን እና ድብርትን የሚቀንስና ምርታማነትና አሰራር ለማሳደግ ይጠቅማል፡፡ ባለአራት የአቀማመጥ ዘዴዎች መቀያየር የሚሉ በመሆናቸው በሁሉም ኦፕሬተሮች ፍላጎት የሚያመቹ ናቸው፡፡

ቅድሚያ ደህንነት
በስተቀኝ በኩል ባለው አንድ መስኮት ላይ በተንጣለለ ሰፊ መስታወት ዙሪያውን በሙሉ በቀላሉ ያለምንም የእይታ ግርዶሽ ማየት ይቻላል፡፡ ባለሶስት ፍሬም መዋቅሩ ከቀድሞዎቹ ሞዴሎች ሶስት እጥፍ የተሻለ ሲሆን ይህም ለኦፕሬተሩ ጫጫታና ንዝረትን ይቀንሳል፡፡ ምቾት እንዲሰጥ ተደርጎ የተገጠመው መቀያየር የሚቻለው መቆጣጠሪያ ንድፉ ትክክለኛውን ኦፕሬት ማድረጊያ ዘዴ ለመምረጥ ቀላል እና ምቾት እና ደህንነትን የሚጎለብት ነው፡፡

Specifications :

  • ዝርዝር መግለጫ:- :
  • ሞዴል:- :
  • ሞተር:- :
  • ጉልበት:- :
  • ክብደት (ኪግ):- :
  • :

Available in :

  • ኢትዮጵያ