ስለእኛ

ሰዒድ መሐመድ አል ጋንዲና ልጆቹ (ኤስኤምኤጂ) መቀመጫውን በዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ያደረገ አንዱ በክልሉ ከፍተኛ የፈጠራ ክህሎት ከሚታይባቸው ንግዶች አንዱ ነው፡፡ ኤስኤምኤጂ ድጋፍ፣ ክፍሎችና አገልግቶችን በደረሱበት ከፍተኛ የእድገት ቅልጥፍና ደረጃ የሚያቀርብ ሲሆን ከ200 ሰዎች በላይ ቀጥሮ በማሰራት ላይ ይገኛል፡፡ ኤስኤምኤጂ የአል ጋንዲ አውቶ ግሩፕ በመላው ጂሲሲ እና ምስራቅ አፍሪካ በርካታ ስፍራዎች ከ1000 ሰዎች በላይ ቀጥሮ በማሰራት ላይ የሚገኝ የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ግዙፍ ማኀበር ነው፡፡ ኤስኤምኤጂ በቅርብ ዐመታት በአዳዲስ ሐገራት በተጨባጭ በመስፋፋት ላይ ይገኛል፣ ከጂሲሲ ባሻገር ምስራቅ አፍሪካን እና እስያን በማካተት የንግድ ይዞታውን በማሳደግ ላይ ይገኛል እንዲም በአለማቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ታዋቂነት ባላቸው አምራች ድርጅቶች ፋንታ ሙሉ ክትትል ያደርጋል፡፡ እያንዳንዱ ሞዴል የተገነባው በከፍተኛ የምቾት፣ የደህንነት እና የብርካቴ ደረጃዎች ሲሆን በአከፋፋይ መስመሮቻችን በሙሉ የግንባታ መሳሪያዎችን፣ አውቶቡሶችን፣ ለቤተሰብ-ጓደኛሞች የሚሆኑ ተሸከርካሪዎችን፣ የቅንጦት መኪኖችን፣ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ተሸከርካሪዎችን፣ የኪራይ መፍትሔዎችን፣ የባህር ቁሳቁሶችን፣ የሐይል ማመንጫዎችን፣ እና ብዙ ብዙ ልናቀርብ እንችላለን፡፡

በኤች.ኢ ሰዒድ መሐመድ አል ጋንዲ ጠንካራ አመራር እና አቅጣጫ አልጋንዲ አውቶ ግሩፕ ለጥራት ስራ አመራሩ የአይኤስሶ  9001 ምስክር ወረቀት፣ ለአካባቢ ስራ አመራር ስርአት አይኤስሶ 14001፣ ለስራ ላይ ጤና እና ደህንነት ኦኤችኤስኤኤስ 18001፣ ለደንበኛ እርካታ አይኤስሶ 10002፣ እና ለመረጃ ደህንነት አይኤስሶ 27001 ተሸላሚ በመሆን ስኬትን ተቀዳጅቷል፡፡ እነዚህ ምስክር ወረቀቶች የደንበኞችን ልምድ ለማሳደግ እንዲረዳ እና ለሰራተኞች አስደሳች የሆነ የስራ አካባቢን ለመፍጠር እንዲረዳ አለማፍ ደረጃ ያላቸውን ምርቶች እና አገልግሎቶች በማቅረቡ ረገድ የንግድ ልዕቀት እንዲሁም የጥራት ገፅታን ዕውን ለማድረግ ያሳየውን ከፍተኛ የስራ ላይ ርብርብ ዕውቅና ለመስጠት የተሰጡ ናቸው፡፡ የመለኪያ ምስል፡፡

አል ጋንዲ አውቶ ግሩፕ የተባበሩት አረብ ኢሜሬትን በቀጣይነት አለማቀፍ ምርቶች እና አገልግሎቶች በማቅረቡ ረገድ ደረጃ በደረጃ የሚያድግ ገበያ የማድረግ ራዕይ ይዞ የተነሳ ማኀበር ነው፡፡ በአንድ ራዕይ፣ በክልሉ በኩል ሰዎች መገናኘት እንዲችሉ ማብቃት እና የተሻሉ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ድጋፍ በማቅረብ የደንበኞቻችንን ህይወት ማሻሻል የሚለውን ግባችንን ለማሳካት ዘብ እንቆማለን፡፡ በዚህም እንኮራለን፡፡ ለስኬታችን መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ ከሰራተኞቻችን፣ ተባባሪዎቻችን፣ አቅራቢዎች፣ እና ከአብዛኛው ደንበኞቻችን ጋራ ግልፅት የሰፈነበት ግንኙነት በመመስረት እናምናለን፡፡ ውጤቶቹ ያረጋግጡታል! ስለቡድኑ ይበልጥ ለማወቅ የሚከተለውን የመረጃ መረብ ይመልከቱ www.alghandi.com::